ዜና


የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባህል፣ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ
በስሩ ከሚገኙ የ11 ዞንና የሶስት ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎች ጋር በ2004 ዓ.ም ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ መከረ
ጎንደር በግማሽ አመቱ አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ መሪነቱን ይዛለች
የክልሉ ባህል፣ቱሪዝምና ፓርኮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሰይድ የጎንደር ከተማን አስተዳደር እና የቱሪዝም ልማት ስልቱን አወድሰዋል፡
ዜና- ቱባ ድህረ ገጽ የካቲት 9/2004 ዓ.ም
አቶ ሙሉጌታ ሰይድ 
የአማራ ብ/ክ/መንግስት ባህል፣ቱሪዝምና ፓርኮች ቢሮ ኃላፊ


 የካቲት 7 እና 8/2004 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በዳንግላ ከተማ በተካሄደውና ቢሮው የየዞንና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎችን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም በገመገመበት በዚህ ጉባኤ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያም ምክክር ተደርጓል፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በባህል እና ቱሪዝም ልማቱ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት እያሳየ በመጣው የአማራ ክልል በተለይም  በቢሮው እና በክልሉ ባሉ ዞንና የከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎች መካከል ያለው ግንኙነት እየጠነከረ መጥቷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ እርስ በእርስ ሴክተሩን ለማልማት የሚደረገው ውድድር የሃገሪቱ ቱሪዝም ላይ በተጨባጭ የሚታይ አሻራውን እያሳረፈ እንደሆነ ለማየት ተችሏል፡፡ የጎንደር ካርኒቫል፣ አሸንዳና በቅርቡ የተደረገው የአዊ የባህል ትእይንት ለዚህ ማሳያ ነው፡፡
የ2004 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ በአማራ ክልል የሚገኙ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች በደረጃ እንዲቀመጡ አስችሏል፡፡በዚህም መሰረት ከ11 የዞንና ከ3 ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያዎች፡-
Ø      የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ 1ኛ
Ø      የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ 2ኛ
Ø      የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ 3ኛ
Ø      የዋግኽምራ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ 4ኛ
Ø      የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ 5ኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡ ደረጃውን የተጎናጸፉት  በግማሽ ዓመቱ ባከናወኑት ተግባር ነው፡፡
የክልሉን የቱሪዝምና ባህል ልማት በተመለከተ በርካታ ሃሳቦችን ለጉባኤው ያካፈሉት የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ሰይድ በተለይም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴክተሩ እንዲለማ እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አወድሰው የግምገማ መድረኩ የተሳኩ ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት እንዲሆን ጠቁመዋል፡፡ ጎንደር ከጥር 9 እስከ 13/2004 ዓ.ም ለ2ኛ ያካሄደችው ካርኒቫል እጅግ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡